እስቲ በዚ ፈገግ በሉ 😃😁😆 ከእለታት አንድ ቀን በትልቅ ጫካ ውስጥ ሁሉም የዱር አራዊት 🦣🦧🐅🦍በተገኙበት ትልቅ ድግስ ይዘጋጃል (ለጊዜው አዘጋጁም : ድግሱም ሰርግ ይሁን መልስ አሊያም ልደት ባይታወቅም) በግብዣው የተለያዩ የምግብ 🍐🍇🥘🥮እና የመጠጥ☕️🍸🥂🍹🧋🥤 አይነቶች ነበሩ። ነገርግን ድንገት የወይን ጠጅ ያልቅባቸውና ሁሉም ይተክዛል። ለግብዛው ድምቀት የወይን ጠጅ ማምጣት የግድ ስለሆነባቸው ለማምጣት ይስማማሉ። ግን ማን ይሂድ? ሁሉም ፈቃደኛ አልሆኑም ስለዚህ እጣ ለማውጣት ይስማማሉ ።... እጣው ሲወጣ እጣው ኤሊ ላይ ወደቀ.... ከዛም ኤሊ 🐢🐢ሄደች።.... ረጅም ሰአታት አለፉ ሁሉም ማዛጋት🥱🥱😴 ጀመረ (አስቡት እነ አንበሳ : ዝሆን🦕🐘🦋🐌🦍.......... ስያዛጉ ) ኤሊ 🐢ግን አሁንም የለችም። ከዛ በጣም ተናደው ሁሉም መቆጣት😡 🥶እና መውቀስ ጀመሩ ።... ከዛም በዝግታ በሩ ተከፈተ... ማን ቢሆን ጥሩ ነው?... ኤሊ🐢🐢...በውሸት ፈገግታ 😏🤪ሲቀበሉኣት እሷ ምን አለች መሰላቹ....ከናንተም ብሶ ትሳደባላቹ እንደውም አልሄድም😂😂😂😁😁
18
Views
0
Likes
0
Comments
0
Shares