በአፋር ህዝብ ዘንድ የመጨረሻው ትልቁ ስጦታ የሆነውን "ሴት ግመል ከነልጇ !!" የክልሉ ፕሬዝዳንት ሀጂ አወል አርባ ለመኩሪያ ሀይሌ ( ዶ/ር ) በስጦታ መልክ አበረከቱላቸው ። ሰመራ ፣ ህዳር 8/2018 (አፋ.ብ.መ.ድ) በዛሬው ዕለት በአፋር ክልል የመሶብ(ኮራ) አንድ ማዕከል አገልግሎት ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል ። የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮምሽን ኮምሽነር የሆኑት ዶ/ር መኩሪያ ሀይሌ ዛሬ በአፋር ክልል በተመረቀው የመሶብ(ኮራ) አንድ ማዕከል አገልግሎት ላይ ማዕከሉ ተገንብቶ እስኪያልቅ ከመጀመሪያው ጀምሮ ፕሮጀክቱን በቅርብ ሆነው እየተከታተሉ እና እገዛ በማድረግ ለፕሮጀክቱ የተሳካ አፈፃፀም ላበረከቱት የላቀ አስተዋጽኦ ከአፋር ክልል መንግስት የምስጋና ስጦታ ተበርክቶላቸዋል ። ስጦታውን ያበረከቱላቸው የክልሉ ር/መስተዳድር ሀጂ አወል አርባ ሲሆኑ በአፋር ህዝብ ዘንድ የመጨረሻው ትልቁ ስጦታ የሆነውን "ሴት ግመል ከነልጇ (Areyonta) " አበርክተውላቸዋል ። በአፋር ባህል ግመልን በስጦታ መልክ መስጠት የተለመደ ባይሆንም ለግለሰቡ ያላቸውን አክብሮትና ፍቅር በቃላት መግለፅ በሚያቅታቸው ደረጃ ላይ ሲደርሱ እጅግ የሚሳሱላትን የምግብም የመጓጓዣም ጠቀሜታ ያላትን ግመልን በስጦታ መልክ ያበረክታሉ ። ሆኖም ግን " ሴት ግመልን ከነልጇ " በስጦታ መልክ የሚያበረክቱት ለግለሰቡ ያላቸው አክብሮትና ፍቅር ከሁሉም ነገር በላይ ሲሆንባቸው እና የኔ ንብረት ያንተ ነው የኔ የሆነ ሀብት ሁሉ ያንተም ነው ብሎ ለመግለፅ የሚሄዱበትን የውዴታ ርቀት የሚያሳይ ነው ። ኮምሽነር ዶ/ር መኩሪያ ሀይሌ የመሶብ አገልግሎትን ለአፋር ህዝብ በማበርከት እና የህዝቡን የመልካም አስተዳደር ችግር ለመቅረፍ ብሎም የተቀላጠፈ ዘመናዊ ምቹ አገልግሎት እንዲያገኝ በማስቻል ላደረጉት ላቅ ያለ አስተዋፅኦ የአፋርን ትልቁን ስጦታ እንዲበረከትላቸው አስችሏቸዋል ። ኮምሽነሩም በስጦታው እጅግ እንደተደሰቱ ገልፀው ለአፋር ህዝብ እና ለክልሉ መንግስት ምስጋናቸውን አቅርበዋል። አፋር ብዙሀን መገናኛ ደድርጅት
18
Views
0
Likes
0
Comments
0
Shares